ውድ ፓስተር ቄስ ቶሎሳ ጉዲና

ድምጾትን ክፍ አድርገው በጨለማው ላይ ሳይደራደሩ ወንጌልን እየስበኩ ስላለና: በዘረኝነት የኢትዮጵ ህዝብ ተክፋፍሎ ፓለቲክኞች ጥላቻን : ዘረኝነትን: ህዝቡን ሲመግቡ : እርሶ ድምጾትን ክፍ አድርገው በሁሉ ቦታ ፍቅርን በቀባበልን አንድነትን እያሳዩ እያስተማሩ ስላለ እግዚአብሔር ቀሪ ዘመኖትን ይባርክ እንላለን::

ለብዙ ዘመናት ክኢየሱስ ጋር ተጉዘው ወንጌልን ለብዙዎች እንዲደርስ : ስዎች ኢየሱስን

እንዲተዋወቁ ምክንያት ስለሆኑ

እግዚአብሔር ቀሪ ዘመኖትን ይባርክ! እግዚአብሔር ክፊቶ ይውጣ!

ShineOn TheDarkness

ዳንኤል ታምራት

ውድ ፓስተር ታምራት ሃይሌ

አንተ ለብዙዎች አባት ነህ:: ወደ 400 ገፀ የሚጠጋውን ሙሉ የህይወት ታሪክህን የፃፍክውን መጽሐፉ አንብቤዋለሁ:: እግዚአብሔር የሚወደውን ስው በሚወደው መንገድ እንደሚመራው በአንትም ህይወት የእግዚአብሔርን እጆች : ምህረቱን : ጥበቃውን ባለፍከው መንገድ ሁሉ እግዚአብሔር ክአንተ ጋር መሆኑን አይተናል:: ስላወጣህ ተራራ ስላሻገረህ መክራ ተመስገን እንጂ ምን ልበል ስትል በመስጋና ውስጥ ድል እንዳለ ለትውልድ አሳይተሃል::

እግዚአብሔር ባሳለፈህ መንገድ ሁሉ የዘመርካቸው ትውልድ ተሻጋሪ በሆኑ ዝማሪዎችህ ትውልድን አቅንተሃል : አድራሻችን መስቀሉ ስር መሆኑን አሳይትሃል: እግዚአብሔር ማወቅ ክሁሉ ይበልጣል…. ብለህ የስው ክንቱ መሆኑን በህይወትን ገፀታ አሳይተሃል:: እግዚአብሔር በትግስት መጠበቅን በሄድክባቸው መንገዶች ለትውልድ አሳይተሃል::

ምን እሱ ብቻ በተለያዪ ግዜ በዘመርካቸው መዝሙሮች :በትግስት ጠብቀው : ክኢየሱስ ጋር ንሮ ይሻለኛል: ይህን ኢየሱስሴን ምል ላድርገው ብለህ : የኢየሱስን ክብር: ንግስና ምድርና ሞላዋን በእጁ መያዙን በዝማሬዎችህ ኢየሱስን አግንነሃል::

አንተ ለብዙዎች አባት መካሪ መሪ ነህ:: እውነት በማይመስሉ ባሳለፍካቸው አስቸጋሪና ውጣ ውረድ ህይወት :ባለፍክው መንገዶች ሁሉ ለብዙዎች ምሳሌ ሆነሃል:: ብዙዎች የእግዚአብሔር መንግስት እንዲቀላቀሉ ምክንያት ሆነሃልና:-

መጽሐፈ ኢያሱ 1:9 “በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”

እግዚአብሔር ክአንተ ጋር ነውና : ፀና: አይዞህ አትፍራ ::እግዚአብሔር ብድራቱን ይክፈልህ: እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንህን ቤተስብህን አገልግሎትህን ይባርክ እንላለን::

“ Rebuilding What Is Broken”

Shine On The Darkness

በጨለማው ላይ እናብራ

ዳንኤል ታምራት

ውድ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን

ረጀም ማራቶን ሩጫ የሚሮጡ ሯጮች : ትኩረታቸው ክጎናቸው ለሚያጨበጭብላቸው ወይ ለሚስድባቸው ተመልካቾች ሳይሆን መድረሻቸው ላይ አድርገው እንደሚሮጡ: ሁሉ: አንተም… ወንጌላዊ ያሬድ ረጀም የክርስትና ሩጫህን ኢየሱስን እየተመለክት በትግስት እየሮጥክ ስላለ :እንደ አንተ ያሉ አባት መካሪ አስተማሪ እግዚአብሔር ስለስጠን አናመስግናለን::

ድምፀን ክፍ አድርገህ (Golden Oil Ministry) በጎልደን ኦይል ሚኒስትሪ ንፁ ወንጌልን ለትውልድ እያስተማርክ: በተስጠህ ዘመን ኢየሱስን እያጎላህ: ለትውልድ ተሻጋሪ የሆኑትን የተለያዩ መጽሐፍቶችን በመፃፍ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን መስላ እንድትታይ እያደረግ ላለው ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክህ::

በተለያዩ እርሶች ላይ መልካም ሕሊና፦ የሮሜ መልእክት:የማካፈል መሥዋዕት፦የማይለወጥ መገለጥ:- እግዚአብሔርን መምስል…. ሌሎችም ትምህርቶችን በማስተማር ትውልድን በመቅረፀ ስላለህ ስለ አንተ እግዚአብሔር እንባርካለን::

ሃገር ብዙ ግራ በተጋባችበት ወቅት ሁሉ: ሀገርን ቤተክርስቲያን ይጠቅማል በምትለው ጉዳይ ላይ ድምፀህን ክፍ አድርገህ እንደ ክርስቶስ አምባሳደር እየስራህ ረጀም ሩጫህን ኢየሱስ ተመልክተህ እየሮጥክ ስላለ እግዚአብሔር አንተንም ክጎንህ የቆሙ ቤተስቦችህን :ቀሪ ዘመንህን ይባርክ እንላለን::

አንተ ለወንጌል ሯጭ አምባሳደር ነህና በርታ!

እግዚአብሔር ይባርክህ::

“ Rebuilding What Is Broken”

Shine On The Darkness

በጨለማው ላይ እናብራ

ዳንኤል ታምራት

ውድ ዶክተር አዳም ቱሉ

በአለማችን ማህበረስብንና ሀገር ላይ ተፀኖ ያደረጉ ስዎች ክሞቱ በውሃላ ብዙ ሲነገርላቸው  ስምተናል:: አንዳንዶች የታደሉ በህይወት እንዳሉ  ለስሩት በጎ አድራጎት ኖሼል ሽልማት ይሽለማሉ::

ዶክተር አዳም :-ብዙዎቻችን አንድ የተስጠጠን መክሊት ለመስራት በተቸገርንበት ወቅት: መክሊታችንን እየቀበርን ባለበት ስአት : አንተ ግን በሁሉም ዘርፍ ቤተስብን በተስጠህ መክሊት እየነገድክ ምሳሌ ሆነሃል::ትውልድን ቤተክርስቲያንን ማህበረስብን:ሀገርን ይጠቅማል : በሚሉ ጉዳዪችና :ቤተክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አምባሳደር ተፅኖ መፍጠር አለባት በምትላቸው ዘርፎች ሁሉ መልካም አስተዋጾ እያደረግ ስላለ እግዚአብሔር ይባርክህ: ዛሬ በህይወት እያለህ ልናበረታታህ እንወዳለን::

ብዙ ክምትስራቸው አስደናቂ ስራዎች መካክል አንዳንዶቹን በጥቂቱ ለማስታውስ ያሃህል:-

*በኢትዮጵያውያ ማህበረስብ ብዙ ትኩረት ያልተስጠውን በአካል ጉዳተኞች ላይ ትኩረት ስጥተህ : ወደ ፊት እንዲመጡ : እግዚአብሔር በውስጣቸው ብዙ አቅምና ችሎታ ማስቀመጡን እያሳወክ: ክሌሎች ጋርም በመተብባበር በበለጠ የሚታገዙበትን በጽናት ኢንስቲትዩት ስር : እየስራህ ስላለህና

* በህፃናትና በታዳጊ ወጣቶች ላይ በእውቀትና እግዚአብሔር ፈርተው እንዲያድጉ : የትምህርት እገዛ : ስንበት ትምህርት የጥምቀት እና የደቀ መዛሙርት ትምህርቶችን በማስተማር ድርሻህን በመወጣት

*ጎልማሶች እና ትልልቅ ስዎች እግዚአብሔር በትክክል አውቀው እግዚእብሄርን እንዲያገለግሉ አጫጫር የስነ መለኮት ትምህርት እንዲማሩ በማስተባበር: እቅድ በማውጣት :በመስራት ለአማኙ የእውቀት መስረት በማስቀመጥ እየስራህም ነው::

*ክዚህ ተጨማሪ እግዚአብሔር ውስጥህ ያስቀመጠውን አውጥተህ  የተለያዩ መጽሐፉቶችን  በመፃፍ እንደ:-የባላደራነት ጥሪ: የለውጥ ጩኸት ሌሎችንም መጽሐፉቶች በመጻፍ በተስጠክ እውቀት ሁሉ ማህበረስብንን እያገለገልክ ነው::

ዶክተር አዳም ለብዙዎች ምሳሌ አጋዥ ሆነሃልና እኛ ኮርተንብሃል! እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንህን የምትስራቸውን ስራዎች ሁሉ ይባርክ:: 

keep shining Jesus

“ Rebuilding What Is Broken”

Shine On The Darkness

በጨለማው ላይ እናብራ

ዳንኤል ታምራት

ለውድ ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ

በአለማችን ጀነራል :ብርጋዴል ጀነራል ኢታማጆር ሹሞች አሉ:: አንተ የክርስቶስ አካል ያለ ነውርና ነቀፋ ሆና እንድትታይ ለትውልዱ : ለአለምና : ጨለማው :እየስማ ድምፀን ክፍ አድርገህ :- ቤተክርስቲያን ኢየሱስን እንድትመስል : ድምፀህን ክፍ አድርገህ አስምተሃል::አንዳዶች በኢየሱስ ስም ንግድ ሲያጦጡፋ ድምፅህን  ክፍ አድርገህ ቤቱ የፀሎት ቤት እንጂ ፈውስ በገንዘብ የሚገዛ አለመሆኑንና ቤተክርስቲያን ንፁ ወንጌልን እንድንስብክ በድፍረት አስተምረሃል:: 

ዘረኝነትን ኮንነሃል::አንተ ክእግዚአብሄር ጄኔራሎች አንዱነህ::

አንዳንድ በመሪነት የተቀመጡ ክአንድነት ይልቅ ልዩነታችንን ሲያጎሉ :አንተ ግን : ክሚለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ብዙ ናቸው ብለህ በተስጠህ ዘመን አንድነትን :ይቅርታን :መቀባበልን አስተምረሃል አሳይተሃል::

ክብዙ ጀነራሎች አንዱ ነህ:: ትውልዱ ኢየሱስ እንዲወድ እንዲክተል ለትውልድ ምሳሌ ሆነህ አስተምረሃል አሳይሃል: መርተሃል::

2 ጢሞቴዎስ 3:10-17 ይህ ክፍል በአንተ ውስጥ አይተነዋል::

ቀሪ ዘመንህን  እግዚአብሔር ይባርክ::

“ Rebuilding What Is Broken”

Shine On The Darkness

በጨለማው ላይ እናብራ

ዳንኤል ታምራት

ውድ ፓስተር ተስፋዪ ጋቢሶ

ሃገሮች የሃገሮቻቸውን በጎ ገፀታ ለማሳየት አባሳደሮቻቸውን በሌሎች ሃገሮች ያስቀምጣሉ:: ግሩም አባሳደሮች አሉ የተወከሉትን ሃገር መልእክት በትክክል የሚያስላልፋ የተላኩበትን ሃገር በሚግባ የሚወክሉ:: ውድ ፓስተር ተስፋዪ ጋቢሶ : አንተ ክብዙዎች አንዱ ምርጥ የኢየሱስ አምባሳደር ነህ::

በስደቱ ዘመን ለክርስቶስ መክራን ስደትን ተቀበለህ ኢየሱስን ያልካድክ:- ተስፋ በማይታይበት በስደቱ ዘመን ህዝብን አበዛ ያገሪቱንም ወስን አስፋ ብለህ ዘምረህ ተስፋን አሳይተሃል:: እስራቱን እና መክራውን ክብዙዎች ጋር ተጋርተህ እንደ ኢየሱስ አምባሳደር ለዚህ ትውልድ ምሳሌ ሆነሃል:: ለብዙዎችን አባት ነህ:: ብዙዎች ክድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን እንዲመጡ ምክንያት ሆነሃል:: ሩጫህን ኢየሱስን ብቻ አይተህ በሮጥክባቸው ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክህ::

ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ መዝሙሮችህ *ግሩም አባት ነህ የምትራራ* ባለፍኩበት መንገድ ለኔ ተጠንቆ* ሀጢያተኞች በደለኞች ሳለን የእግዚአብሔር ፍቅር በክርስቶስ አየን … በሚሉት መዝሙሮችህ የእግዚአብሔር ፍቅር ለትውልድ ያስተላለፍክበት: አስገራሚዎች ናቸው::

ሃጢያታችን ደምስስህ የክብርህ ማደሪያ መቅደስህ አረክን በሚለውም መዝሙርህ ሁላችን ምን እንደሆንን በመዝሙርህ አሳይተሃል::

ምን እሱ ብቻ……..”ምህረቱን ልዘምር ቅኔን ልቀኝለት” ብለህ ኢየሱስ አጉልተሃል: በጨለማው ላይ አብርተሃል::

“ያይሃል ያይሃል ያይሃል ያይሃል

ያይሃል ኢየሱስ ያይሃል

ያይሃል በእውነት ያይሃል

የአንተ ነገር ይገደዋል

ሊታደግህም ይመጣል”

አንተ ምርጥ አምባሳደር : አባት ነህ::

እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንህን ይባርክ እንላለን::

በጨለማው ላይ እናብራ

ShineOn TheDarkness

ዳንኤል ታምራት

ውድ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው 

በዘመናችን በአለም ላይ ብዙ ታላላቅ ስዎች ተነስተው የትውልድን ሞራል የገደሉ : ሃገርን ወደ ድህነት የወስዱ : ብዙ እናትና ባቶችን ያስለቀሱ እንዳለሉ ሁሉ:

በዛኑ ያህል የትውልዱን እንባ ያበሱ: እውቀትንና ፈጠራን ያስተላለፋ : ማህበረስባቸውንና ሃገርን ቀና ያደረጉ : እንባ ያበሱ መልካም ስዎች አሉ:: እርሶ ከመልካሞቹ አንዶ ኖት::

በተቀመጡበት አጭር አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ትውልድ ለመቅረፀና እውቀት ለማስግኘት ዋና መስረት የሆነውን ትምህርት ቤቶችን በማስገባት ለትውልዱ ትልቅ መስረትን ጥለዋል::

በትምህርት ቤት እጥረት ወይንም እርቀት ምክንያት ልጆቻቸዉን ወደ ትምህርት ገበታ 

መላክ ያልቻሉትን ቤተስቦችን እንዲልኩ እድሉን ፈጥረዋል:: 20 ትምህርት ቤቶችን በማስገንባት በትምህርት ቤቱ በዉስጡ የአስተዳደር ህንጻ፤የመማሪያ ክፍሎች ፤ላብራቶሪ የኮምፕዩተር ፤የቤተ መጽሀፍ ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን ያካተተ ግንባታዉ በማስገንባት እስከዚህ ቀን ድረስ ያለቁትን በማስመረቅ ላይ ይገኛሉ::

በተጨማሪም ብዙ ተማሪዎች ዩኒፎርም ፣ቦርሳና የሙቀት መለኪያ መሳሪያወችን በስጦታ አበርክተዋል።

ለሌሎች በመራራት :ይህ መልካም ድርጊቶ በሁሉም አቅጣጫ እንደሆነ አይተናል:: በቅርቡም የአይነ-ስውራን ተማሪዋች የላፕቶፕ ስጦታ በማበርክት: አካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ በማድረግ: የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለልበ-ብርሃኖቹና ለህጻናት ማሳደጊያ፤ በማድረግ በቅንነት ለሚመለክትዋት ሁሉ በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ትልቅ መስረት ለትውልድ እያስቀመጡ ነው::

የፈረስውን በመገንባት : የቆሽሽውን በማጽዳት : የተቸገረውን በመርዳት :

የበጎ አድራጎት ፈቃደኞችን አስተባብሮ ችግኞችን በመትከል አረንጓንዴ አሻራ አስቀምጠዋል፡፡

በእርሶ ጽ/ቤት የተገነባው ብርሃን የሕፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ግንባታው ተጠናቆ የዘውዲቱ መሸሻ የሕፃናት ማሳደጊያን የቃጠሎ አደጋ የደረሰበትን የሕፃናት ማሳደጊያ ለመደገፍ ቃይህ ማዕከል 72 ሰዎችን የሚያስተናግድ ቤተ መጻህፍት መመገቢያ አዳራሽ: ማብሰያ: የአስተዳደር ቢሮ: 96 ህፃናትን የሚያሳድሩ መኝታ ክፍሎች ስርተዋል::

አሁን የምናየውን ጥላቻ አልፈው እርሶ ፍቅርን ስላስዪ: ሌላው ሲያፈርስ እርሶ እና ክአጠገቦት ያሉ ሲገነቡ: አይተናል::

ማረን በሚለው መዝሙሮት ….. እግዚአብሔር ምህረት ጠይቀዋል::

በጨለማው ላይ ማብራቶትን ቀጥለዋል::

በከተለያዩ ለጋሽ አካት ያሰባሰባቸዉን የህክምና እቃዎች እና መገልገያ መሳሪያዎች በእርሶ በክብርት ቀዳማዊት እመቤት በ ጽ/ቤታቸዉ በኩል፡

የህፃናት አልጋ ፤ የደም ማስቀመጫፍሪጆች ፤ ICU አልጋ፤ የላብራቶሪ ማሽኖች በአጠቃላይ አስራ ሰባት (17) የህክምና ቁሳቁሶች ተበርክተዋል፡፡ የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በአጠቃላይ ክ ግማሽ ሚሊዪን ብር በላይ የህክምና እቃዎችን ለተለያዩ ሆስፒታል ድጋፍ ሲያደርጉ ይታወሳል፡:

በተስጦ አጭር ግዜ የብዙ ቤቶችን አሳርፈዋል : ለሃገር መስረትን ጥለዋል: ትውልድን የሚቀርፀ መስረት ጥለዋል::

ብርሃናችሁ ለአለም ሁሉ ይብራ እንደተባልው: መልካም ብርሃኖት በስዎች ፊት እየበራ ስላለ: ኮርተንቦታል::

Cash App
240-796-8762
#ShineOnTheDarkness